የእስከ አሁኑ አይበቃም?

ሣምራዊት ንጉሤ

አንድ ልብሱ የቆሸሸ ሰው የሚቀመጥበትን ወንበር ወይም መሬት ንፁህ እንደለበሰ ሰው ልብሱ እንዳይቆሽሽ ቢጠርግ፥ ወይም ለመቀመጥ ቢጠየፈው ምንድነው የምንለው?

“ደሞ ንፁህ እንደሆነ ይጠየፋል እንዴ?”

አይደል?

በህይወታችን ውስጥ ሆነ ብለንም ይሁን ሳናውቅ ስህተቶችን እንሰራለን። ተምረንባቸው ከአለፉት ስህተቶቻችን እንቆጠባለን።ታዲያ ዛሬ ላይ ያንን ማንነት ስንጠየፈው ቢያዩን “ምነው እንደዚህ አልነበርሁም አልክ?” እንባላለን።

ንፁህ የለበሱ ሰዎች የሚቀመጡበትን ቦታ የሚጠርጉት እንዳይቆሽሹ ነው!

ንፁህ ያልለበሱ ሰዎች ቦታውን የሚጠርጉት ግን ንፁህ ከሆነ ቦታው በእነሱ እንዳይቆሽሽ፥ ወይም ደግሞ የቦታው ንፁህ አለመሆን ይባስ እንዳያመነችካቸው ይሆናል….።

የጭንቅላታችን፥ የልባችን መቆሸሽንስ መቼ ነው የምናፀዳው?

መቼ ነው? “የእኔ ይበቃል። ሌሎቹም በእኔ ልክ ያልሆነ አስተሳሰብ ውስጥ እንዳይገቡ ልጠብቅ” የምንለው?

መቼስ ነው የእስካሁኑ ስህተቴ ይብቃ ብለን እራሳችንን ከቆሻሻ ሀሳቦች የምንጠብቀው?

የእኛ አይበቃም?

እኛ ባለፍንበት ሰው ካላለፈ አናርፍም?

የሰማነው ከዘገነነን ለምን ለሌላው እንደግመዋለን?

ያየነው ካስጠላን ለምን ለሌላው እናሳየዋለን?

በውስጣችን ያሰብነው ነውር ከሆነ ለምን ተናግረን ነፍስ እንዘራበታለን?

መቆሸሽንም ቆሻሻንም ማንም አይወድም። ለልብሳችን፣ለጫማችን….የምንፀየፈውን ቆሻሻ ለልባችንም እንፀየፈው!

                  የወር ሰው ይበለን!

ተያያዥ ልጥፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *