ጠይም ትዝብት ዚቅ

ፋሲካው ጌታቸው ገሰሰ

ትናንትና ማታ…!
እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ግፊያ ያባዘተው፣ ልብ አልባው ከተማ
በታክሲው ጥሩንባ፣ በወያላው ጩኸት፣ እዡን እየደማ
የየቡና ቤቱ፣ ለእሳቱ ወራዙት፣ የዕርቃን ጥሪ ዜማ
ተሻሽቶ መውረግረግ፣
ስልት የቀቡት ዕብደት፣ ያን ፍትወት ሲጠማ
ብራተ ኮከብ ጋር…
የወርቅ ወጨት መሳይ፣ በሰማዩ ቀፈት፣ ጨረቃይቱ በቅላ
እስኪ ተመልከቺ፣
ጽጌሬዳ አበባ፣ አውሎ ጋር ስትደንስ፣ አንጀቴን ስትበላ፤


በየመንገዱ ጠርዝ፣
ጡት የናፈቀው ልጅ፣ ቤንዝል የሚጠባ
ጋሽዬ በማርያም፣ ብሎ ሲለምነኝ፣ ሀዘን ውስጤ ገባ፡፡
ደግሞ ሌላዋ እናት፥
እራፊ ነጠላ ፣ልጇ ላይ ጣል አርጋ
ሐፍረቷ ጋር ሁና፣ ሁነኛ መስያት፣ እጇን ስትዘረጋ
ሆድ ባሰኝ በእጅጉ፤
ደግሞ ሌላ ጥንዶች፣ ተቃቅፈው ተቋልፈው፣ እየተላላሱ
ካልጠፋው ጎዳና፣ ባጠገቤ ደርሰው፣ ሳይ ሲመላለሱ
ሆድ ባሰኝ ዓለሜ፤


(ይባስ ብሎ…)
ፀሐይ ፈገግታዬን፣ የደመና ኩርፊያ፣ ከልቤ ሲነጥል
ማነህ የሚል ሳጣ፣ እንደ ደራሽ ዝና፣ ቀልብ ራሴን ስጥል
በልበ ቢስ መሃል፣
ነጋዴና ወረት፣ በሽሬታ ተመን፣ ቀልብ ልቡን ሲስት
ልብ የገዛ ሰው ነው፣ ለከውኑ እያሰበ፣ ለዓለሙ ‘ሚሰስት።

ተያያዥ ልጥፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *