ብርሃን ደርበው

Zaf Korachu a post card story By Birhan deribew.

ገብሬ እንደወትሮው ሁሉ ፎጣውን ራሱ ላይ ጠቅልሎ መጥረቢያውን አንግቶ በማለዳ የጀንበሯን መፈንጠቅ ተከትሎ ወደ ሥራው እየገሰገሰ ነው። “እንደው እንደሱ ያለ ዛፍ ቆራጭማ የለም። ገና መጥረቢያውን ሁለቴ ሲያሳርፍበት እኮ ነው ዛፉ ግንድስ የሚለው።” እያሉ ለሥራው ምስክርነትም አድናቆትም ይቸሩታል— የመንደሩ ሰዎች፡፡

የኖረበትና የሚያውቀው ሥራው ኑሮውም ትዳሩም ነው። ማልዶ ይወጣል። ዛፍ ሲጥል ውሎ ጀንበር ስታዘቅዝቅ በመንገዱ ካለች ኮማሪት ጋር አንድ ሁለት ቀማምሶ ወደቤቱ ይገባል፡፡ ዛሬ አለወትሮው አረፋፍዶ ሲወጣ ቁልቁል በመንገዱ በስተግራ በኩል በማቆጥቆጥ ላይ ያሉ ችግኞችን የያዘች መስክ ላይ ገሚሱ ከብት ገብቶ የቀረውም እየገባ ተመለከተ። ይሄን ባየበት ቅጽበት መጥረቢያውን እና ፎጣውን መሬት ላይ ጥሎ ሽመሉን ይዞ ወደ ከብቶቹ ገሰገሰ። ከብቶቹንም ማራወጥ ጀመረ፡፡ ይሄኔ በከብቶቹ መንጋጋት የደነገጠው ውሪ እረኛ ጨዋታውን አቋርጦ ቢያይ ከኋላ ሽመል የያዘ ፈርጣማ ጎልማሳ “ሂጅ!” እያለ ያባርራል፡፡

ኧረ ጋሼ ምን አርጉ ነው ምትላቸው? ሲል ጠየቀው።

ወግድ! ችግኙን እያበላሹት ዝም ብለህ ታያለህ? በል ዳግመኛ ወዲህ ድርሽ እንዳይሉ ብሎ ወደ ኑሮው ተመለሰ፡፡

ተያያዥ ልጥፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *