“የነገ ሰው—” እንዳላብድ ልጅ ሰጠኝ

በሳምራዊት ንጉሤ

አንድ ታሪክ ልንገራችሁ እስኪ። እንዳላብድ ልጅ ሰጠኝ ስላለቺኝ ልጅ…

አንዲት ሴት ናት እንደዚህ ያለቺኝ። “ታውቂያለሽ?” አለቺኝ “ታውቄለሽ እግዚአብሔርን አስከፍቼዋለሁ— ብዙ ጊዜ! እርሱ ግን ሁሌ አብሮኝ ነበር።  ልክ ያልነበሩ ነገሮች በህይወቴ አልፈዋል። በዛ ብቀጥል ኖሮ አብድ ነበር።”

አለቺኝና ወደ ልጅዋ እያየች ፈገግ ብላ “ግን እግዚአብሔር እንዳለብድ ልጅ ሰጠኝ።”

አያችሁ ምን አይነት አምላክ ነው እንደሆነ? ሩቅ ሆነን የሰዎችን ህይወት እያየን እንዲ እንላለን ‘ የእጁቃን ነው የሰጣት!’

እነሱ ደሞ “እግዚአብሔር እንዳልጠፋ ይሄን ሰጥቶ ሰበሰበኝ” ይላሉ።

ሁሌ የስህተት መጨረሻ መውደቅ አይሆንም።አንዳንዴ በስህተቶቻችን ውስጥ በረከቶች ይኖራሉ።  አጥፍተን አጥፍተን አናርፍ ስንለው በራሱ መንገድ ያሳርፈናል። ህይወታችሁን ቃኙት።

እንዴት ነበር?

ከምን መለሳችሁ?

ከምኑስ አወጣችሁ?

ተያያዥ ልጥፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *