የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው………. ።

በሩት ሃብተማርያም

ከማሰሮ የዘገንከው ትኩስ እፍኝ አሹቅ ወደ አፍህ ስታስጠጋው፣ አፍህ እዚህ የከንፈርህ ጥጋት ጋር ስታደርሰው፣ ብር ብሎብህ ያውቃል? ወይ ደሞ መንገድ ላይ ለማታውቀው ሰው በፈገግታ ሰላምታ ሰጥተህ ስታልፍ ፈገግታህ በስንት ሰከንድ ይከስማል? የእግርህን አውራ ጣት የመታህ ትንሽ እንቅፋት ልብ ስር የሚገባ ህመም በስንት ደቂቃ በረደልህ? የጣቶችህን አንጓዎች እያጠፍህለማድረግ የፈጀብህን ቅፅበት በቁጥር ታውቀዋለህ? በህልምህ ያየኸው ውብ ዓለም ልክ ዓይንህን ስትከፍት ለመጥፋት ከብርሃን ይፈጥን አይደል? ልክ እንደዛ ልክ እንደ ሁሉም ፍቅር ይበርድብኛል። በእጄ ሳልይዘው ይሰበርብኛል። ምን ላድርግ?

“ዘንድሮ ፍቅር የለም!” እያሉ በራሳቸው የፍርሃት ድንበር ውስጥ እንዳሉት ሰዎች አይደለሁም። ሰው የተባለ ፍጡር በህይወት እስካለ ድረስ ፍቅር የትም አለ። አይታየንም እንጂ ያያዘን ቀጭን መሳይ ጠንካራ ድር ፍቅር ነው።

አለ ብዬ አምኜው እየኖርኹ ታዲያ ስይዘው ለምን ጥብቅ አያደርገኝም? ስዳስሰው ቁንጥጫው የሚብሰው ለምንድን ነው? ስስመው ለምን ጥርሱን ያገጣል? መጣ ብዬ “እሰይ! እሰይ! ከመጣህ ማርያም ታምጣህ!” ብዬ፣ ከንፈሬ ከማሰሪያው ተፈቶ ፈገግ ሳልል ወዴት ሄዶ ይጠፋብኛል? እንደ ማድጋ ሊጥ፣ ተሟጦ እንደሚጋገር፣ አሟጦ የሚያፈቅረኝ የት ነው?

ሁላችንም፣ እኔም  አንተም ሳንዘጋው የተውነው የትዝታ በር አለን። በቀጭን የምትነፍስ ትላንትን የምትናፍቅ ንፋስ የሚያሳልፍ በር አለን። አሁን ቁጭ ብዬ ሳስበው አጠገቤ የነበሩ፣  ያፈቀርኳቸው ፤ ያቀፍኝ ፤ ሳናይሽ አናድርም ልመናዎች ሁሉ የትዝታቸውን በር መሸጎሪያ እንጂ በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ የራሴ የትዝታ በር የለኝም። ታዲያ ይሄ አያደክምም?

በዓለም ያንተን አይነት ፈገግታ ያለው አይቼ አላውቅም። ፈገግ ስትል ፊትህ ላይ ያለውን ኃይል አልችለውም። እወድሻለሁ ስትለኝ እያንዳንዷን ፊደል ሰንጥሬ ባያት ምንም ማብለጭለጫ ቅመም እንዳልተጨመረበት አውቃለሁ። ፊቴ ስትመጣ የዋህነትን ብቻ ትሰዋልኛለህ። ደስ ትለኛለህ። ዓይኔን ከድኜ እጄን ልሰጥህ እፈልጋለሁ። ታዲያ ግን እፈራለሁ። ፍርሃቴን አሸንፌ ባቅፍህ በማግስቱ ትተወኛለህ። አነሳሴ ጋ አውግተን ሳንጨርስ ወድቄ  እነቃለሁ። እንዲሁ ባይህ ይሻላል። እንዲሁ በሩቅ ብመኝህ ይሻላል። ምኞቴን ሸሽጌ ፤ ምኞትህን ሸፍኜ እንደ ሩቅ ዘመድ ብንተያይ ይሻላል። ላጣህ ስለማልፈልግ ነው ከጠረንህ አፍንጫዬን ያቀብኩት ፤ እቅፌን ያቀዘቀዝኩት ዘላለም በልብህ እንድታቅፈኝ ነዉ። የ40 ቀን እድሌ ትለኝ ነበር አያቴ። ያኔ ታዲያ እስቅ ነበር። 40 እና እድል ምን እንዳቆራኛቸዉ ይደንቀኝ ነበር። አሁን በየቀኑ ሳይገባኝ አልቀረም። የ40 ቀን እድል አለን ሁላችንም። በማይታይ ማተብ አንገታችን ላይ ያለ።

እና ትወደኛለህ?

🎼

ተራራው ሰው፣ ሆኖ ከንፈሬን ባይስመኝ

ተራራው ሰው ሆኖ፣ ጡቴን ባይዳብሠው

ተራራው ሰው ሆኖ፣ ዓይን ዓይኑን ባላይ

ጸሀይ እሞቃለሁ፣ ወጥቼ ከላይ።

.

.

… መናፈቅ ዝም ብሎ ከገላ ላይ የሚጨልፍ ምትሀት ነገር አለው። ማሸጊያው ሳይፈታ ቁጫጭ በልቶት እንደሚያልቅ ከረሜላ እንደዛ ባሉበት ይጨርሳል። ልብን መነሻና፣ መድረሻ አድርጎ ይመላለሳል። ሲናፍቁ ዓይንን ቢከድኑት ማምለጥ ዘበት ይሆናል። እግርን እንዲራመድ ቢያዙት የጉዞው መድረሻው ሳይታወቅ ካሉበት ፈቀቅ ሳይሉ መጫሚያ ያልቃል። ጆሮ ጥኡም ሙዚቃ ቢሰጡት የእሱን ሹክሹክታ ያመጣል። መሃላን ያስረሳና ስለትን ያስመኛል።

… ከናፍቆት ጋር ድብብቆሽ መጫወት ስጀምር፣ ልክ እንደማንኛዉም ተጫዋች ተናፋቂው ተደብቆ ሲቀር ጨዋታዬን አቆማለሁ ብዬ ነበር። የመፈለግ ፅናቴ ተሰብሮ ወይም ሟሙቶ ያለቀ መስሎኝ ነበር።እንደዚህ የተደበቀበትን ጋራና ሰርጣሰርጥ ሁሉ በልቤ አስሳለሁ ብዬ አልነበረም። ልቤ ኩስ ኩስ ብላ ከእግሬ ስር እየተራመደች የምትመራኝና የምታወራኝ ይመስለኛል። እንዴ እሱም ጋር እኔም ጋር ልቤ ልትኖር አትችልም። ሲፈቀር ልብ ይሰ’ጣል ይሉ የለ እንዴ? ታዲያ የኔ ልብ ይቺት ከፊቴ። ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው እንዴ የያዘኝ? የጨዋታ አሸናፊ አለመሆኔ ተሰምቶኝ ነዉ እንዴ? እያልኩ አስባለሁ።

” ሰማሽኝ እቴ አካልሽ ሁሉም እዚህ ነው።  ሀሳብሽ ፤ ህልምሽ ፤ እርካታ እና ስሜትሽ ሁሉም ሰዋዊ ስሜቶችሽ ናቸው እሱ ጋር የተደበቁብሽ። ሰው ሲያፈቅር ሰውነቱን ፣ ሰው የመሆኛ፣ ሰው የመባያ ነገሮቹን ነው አሳልፎ ለሚያፈቅረው የሚሰጠው። አብሬሽ ያለሁት ልብ ተብዬ እንድጠራ የሚያደርጉ ስሜቶቼን ስለወሰደብኝ ነው።” አለች ኩስ ኩስ እያለች።

… ለነገሩ ልክ ናት እላለሁ። ምን ታልሚያለሽ ቢሉኝ ከንፈሩ ስር የማርያም ስሞሹ መሆን አይደል? ምን ታስቢያለሽ ቢሉኝ ንፋስ የራሱን ፀጉር ስንቴ ዳበሰችው? ጨረቃ ለምን አዘቅዝቃ ታየዋለች? እንቅፋት መቶት ይሆን? አንዷ ቁሌታም ስታልፍ አይታ ተመኝታው ይሆን? አንድ ጤነኛ ሰው እንዲህ ያስባል?

…አስቀድሰው ሲጨርሱ እንደሚሰጥ ቁራሽ፤ቤቱ ቢሄድም የሚበላ እንደሌለው ሰው ያቺን ቁራሽ እንደሚያጣጥማት (እንደዛ ናፍቆቱ ይጣፍጠኛል) ፤ የመጨረሻ የጎለተችው ድንች ተሸጦላት ለልጆቿ ራት መግዛት እንደምትፈልግ እናት ገዢን በጉጉት እንደሚጠብቁ ዓይኖቿ (እንደዛ በየቀኑ ለፍቅሩ እጓጓለሁ ) ፤ ረጅም ዓመት በደዌ ተሰቃይቶ ጎኖቹ ሁሉ በቁስል ነደው መተኛት እንደናፈቀው ፣ፈውስ መጣልህ፣ ጎንህ አገገመ ተብሎ የነገ ፈውሱን አስቦ እንደሚጋደም ጎልማሳ (ልክ እንደዛ የፍቅር እፎይታን እናፍቃለሁ)።

… ዓይኔን አልነግረውም። ፍቅርህ ላይመጣ ይችላል ብዬ አልነግረውም።  በሩቁ እያየነው እንደምንኖር አልነግረውም። ጉጉቱን አውቃለሁና ቢጠብቅ ይሻላል።

እጄን “ደረቱን አትዳብስም ፤ አንገቱ ዙሪያም ላትሆን ትችላለህ እኮ” ብዬ እንዴት ላስረዳው?

እግሮቼን “ወዳለበት አትሄዱም፣ ቁሙ!!” ማለት አልችልም። ከእግሬ ቀድሞ የእርምጃ ሀሳቤ የት እንደሚሄዱ ይነግራቸዋል። ማንንም ማዘዝ አልቻልኩም። ሀሳቤን ፤ ህልሜን ፤ ዓለሜን ሰጥቼ ነዋ የወደድኩት። ግን ትወደኛለህ?

Before you plunge headfirst into the world of gaming, it’s crucial to choose your weapon of choice. Are you Team Console or Team PC? Take a moment to assess your preferences and budget, ensuring that your gaming rig is primed and ready for action. Upgrade your hardware, update your software, and set the stage for an immersive gaming experience.

2. Mastering the Controller Commandments:

Every game comes with its own set of rules and controls. Familiarize yourself with the basic commands, get comfortable with your controller or keyboard, and understand the game mechanics. It’s like learning the ABCs before diving into the literary world – a foundation that will serve you well on your gaming odyssey.

Image Not Found

3. Embracing the Noob Spirit:

Welcome, intrepid explorers of the digital frontier! Whether you’re a fledgling gamer or just looking to up your game, this beginner’s guide is your ticket to unlocking the secrets of the gaming universe. Strap in, grab your controller, and let’s embark on this epic journey together. Every game comes with its own set of rules and controls.u003cbru003eFamiliarize yourself with the basic commands, get comfortable with your controller or keyboard, and understand the game mechanics. It’s like learning the ABCs before diving into the literary world – a foundation that will serve you well on your gaming odyssey.

a. Seek Guidance from Mentors

Every game comes with its own set of rules

b. Watch Tutorial Videos:

Every game comes with its own set of rules and controls.

c. Embrace Failure as a Stepping Stone:

Every game comes with its own set

4. Mastering the Controller Commandments:

Welcome, intrepid explorers of the digital frontier! Whether you’re a fledgling gamer or just looking to up your game, this beginner’s guide is your ticket to unlocking the secrets of the gaming universe. Strap in, grab your controller, and let’s embark on this epic journey together. Every game comes with its own set of rules and controls.u003cbru003eFamiliarize yourself with the basic commands, get comfortable with your controller or keyboard, and understand the game mechanics. It’s like learning the ABCs before diving into the literary world – a foundation that will serve you well on your gaming odyssey.

ተያያዥ ልጥፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *